Addis Ababa, Ethiopia
Medical service LEO, Hospital and Diagnostic Desk National Surgical and Anesthesia Program Office, Ministry of Health, Ethiopia, 6 killo Leadership Institute, info@n4pcc.com (+251) 943 151 718
See More Pictures ->
የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ Network for Per Operative and Critical Care ፕሮጀክት ጋር በጋራ ለመስራት ግንቦት 15/2016 ዓ.ም የውል ስምምነት አካሄዷል፡፡ Network for Per Operative and Critical Care ፕሮጀክት እንደ ሃገር በቀዶ ጥገና ህክምናዎች ላይ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የሰርጅካል የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎትን አጠናክሮ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስራት አላማ ያለው ሲሆን በሃገሪቱ ከ40 በላይ ሆስፒታሎችን የሰርጀሪ ህክምናው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአሰስመንት ስራ እየሰራና የታካሚ መረጃ አያያዝን ተደራሽ በማድረግና በማስፋት በጥናት ላይ የተመሰረተ መረጃዎችን መያዝ እንደሚገባ ትኩረት ያለው ነው፡፡ በእለቱ የNetwork for Per Operative and Critical Care ዋና ማናጀር አቶ ኤርሚያስ በላይ እንደገለፁት ሆስፒታሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል ደረጃ ከፍተኛ ስራ እየሰራ በመሆኑ ለሌሎች ተቋማትም የሞዴልነት ምሳሌ የመሆን አቅም እንዳለውና የጥራት ቡድኑን እና የማኔጅመንቱን ክትትልና ድጋፍ አድንቀዋል፡፡ የሆስፒታሉ የPlastic, Reconstructive, and Hand surgery department ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ይገረሙ ከበደ የለውጥ ሃሳቦች በመተግበር እና የኦፕሬሽን ክፍልን ውጤታማነት በመጨመር የታካሚዎችን የቆይታ ጊዜ የሚያቃልልና ውጤታማ የሚያደርግ ስምምነት መሆኑን ጠቅሰው መረጃዎችን በመያዝ የሚቀጥሉት ስድስት ወራት ተሰርቶበት የሚታይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ፕሮጀክቱ የሚያመጣቸውን ለውጦች ለሌላ የስራ ክፍሎች መጠቀም እንደሚቻልና ለፕሮጀክቶች ስኬታማነት የሚቻለውን ጥረት በማድረግ በሆስፒታሉ ያለውን የታካሚ የቆይታ ጊዜ የሚቀርፍ ብቻ ሳይሆን የሚሰሩ የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች የተገልጋይን እርካታ እንደሚጨምሩም የሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዶ/ር ፀጋዮ ገ/ አናንያ አብራርተዋል፡፡